Followers

Thursday, June 9, 2011

የኢትዮጵያ መንግስት 200 ታንኮችን ለመግዛት በ 1᎐7 ቢሊዮን ብር ከዩክሬን ካምፓኒ ጋር ተስማማ::

 ስሪታቸው የቀድሟ ሩስያ የሆኑ T.72   የተባሉ ታንኮችን በመቶ ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ከዩክሬን መንግስታዊ መሳሪያ ላኪ ድርጅት ጋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር መስማማቱኑ የዮክሬኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘግባል:: ስምምነቱ  የዩ ክሬኑ ካምፓኒባለፉት አሰራ አምስታት አመታት ውስጥ ከሽጣቸው  መሳሪያዎች      ትልቅ የ ሚባል መሆኑን ተዘግባል:። እንዚህ ታንኮች በ1970 በሶቭየት ህብረት የተሰሩ የሁለተኛ ትውልድ ታንኮች የሚባሉ ሲሆን የዩክሬኑ ካምፓኒ ዘመናዊ መሳሪያዎችንና የተለያዩ ማሻሻያዎችን አክሎ ታንኮችን እንደሚያስረክብ ይጠበቃል:: የመሳሪያ ግዥው በኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ ጌዜ የተገዛና ትልቅ ሊባል የሚችል ሲሆን በዚህ አመት ብቻ የኤትዮጵያ መንግስት  ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰው አልባ ኧውሮፕላኖችን  ከእስራኤል ካምፓኒ መግዛቱ ይታወሳል:: በተጨማሪም ብዙ ወታደሮችን ወደ ህንድ አገር በመላክ እያሰለጠነ ይገኛል:፡ አገር ውስጥ የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ በነካበትና ግሽበቱ 30% በደረሰበት ሁኔታ እንደዚ ያለ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ያደርገዋል:: ቀደም ብሎ መንግስት በይፋ  የኤርትራን መንግስት ለመጣል   እንደሚንቀሳቀስ ያስታወቀ ሲሆን የአሁኑም መሳሪያ ግዥ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል::በአገር ውስጥ በአባይ ግድብ ምክንያት የተፈጠረውን የህዝብ መነሳሳት በመጠቀም በኤርትራ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳ ይመስላል:: ስሞኑን የመንግስት መገናኛ ተቃማት በኤርትራ ላይ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ያዘጋጁ ሲሆን ከመንግስት ምስጢራዊ አስራር ጋር ተዳምሮ የነዚህ መሳሪያ ግዢ በእሁን ሰአት መሆኑ አነጋግሮኧል :: ምናልባትም ወደፊት እንደሶሪያ መንግስት ለመጠቀም ሊሆን እንደሚችል ይገመታል::