Followers
Blog Archive
Thursday, June 9, 2011
የኢትዮጵያ መንግስት 200 ታንኮችን ለመግዛት በ 1᎐7 ቢሊዮን ብር ከዩክሬን ካምፓኒ ጋር ተስማማ::
ስሪታቸው የቀድሟ ሩስያ የሆኑ T.72 የተባሉ ታንኮችን በመቶ ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ከዩክሬን መንግስታዊ መሳሪያ ላኪ ድርጅት ጋር የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር መስማማቱኑ የዮክሬኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ዘግባል:: ስምምነቱ የዩ ክሬኑ ካምፓኒባለፉት አሰራ አምስታት አመታት ውስጥ ከሽጣቸው መሳሪያዎች ትልቅ የ ሚባል መሆኑን ተዘግባል:። እንዚህ ታንኮች በ1970 በሶቭየት ህብረት የተሰሩ የሁለተኛ ትውልድ ታንኮች የሚባሉ ሲሆን የዩክሬኑ ካምፓኒ ዘመናዊ መሳሪያዎችንና የተለያዩ ማሻሻያዎችን አክሎ ታንኮችን እንደሚያስረክብ ይጠበቃል:: የመሳሪያ ግዥው በኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ ጌዜ የተገዛና ትልቅ ሊባል የሚችል ሲሆን በዚህ አመት ብቻ የኤትዮጵያ መንግስት ቁጥራቸው ያልተገለጸ ሰው አልባ ኧውሮፕላኖችን ከእስራኤል ካምፓኒ መግዛቱ ይታወሳል:: በተጨማሪም ብዙ ወታደሮችን ወደ ህንድ አገር በመላክ እያሰለጠነ ይገኛል:፡ አገር ውስጥ የኑሮ ውድነቱ ጣሪያ በነካበትና ግሽበቱ 30% በደረሰበት ሁኔታ እንደዚ ያለ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ያደርገዋል:: ቀደም ብሎ መንግስት በይፋ የኤርትራን መንግስት ለመጣል እንደሚንቀሳቀስ ያስታወቀ ሲሆን የአሁኑም መሳሪያ ግዥ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል::በአገር ውስጥ በአባይ ግድብ ምክንያት የተፈጠረውን የህዝብ መነሳሳት በመጠቀም በኤርትራ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳ ይመስላል:: ስሞኑን የመንግስት መገናኛ ተቃማት በኤርትራ ላይ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ ያዘጋጁ ሲሆን ከመንግስት ምስጢራዊ አስራር ጋር ተዳምሮ የነዚህ መሳሪያ ግዢ በእሁን ሰአት መሆኑ አነጋግሮኧል :: ምናልባትም ወደፊት እንደሶሪያ መንግስት ለመጠቀም ሊሆን እንደሚችል ይገመታል::
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment